The Orange Door

አማርኛ

መረጃበአማርኛ

ኦሬንጅ ዶር (The Orange Door) ለቤተሰብ ጥቃት እንዲሁም ለህፃናት ደህንነት እና እድገት ድጋፍ ለሚሹ ቤተሰቦች እርዳታ እና ድጋፍን ይሰጣል።

አንዳንድ ጊዜ በቤት ውስጥ ወይም በግንኙነት ውስጥ ያሉ ነገሮች ጤናማ አይሆኑም እናም አንዳንድ እርዳታ እና ድጋፍ ያስፈልግዎታል። The Orange Door እርስዎን ለማዳመጥ እና የሚፈልጉትን ድጋፍ በፍጥነት እና በቀላሉ እንዲያገኙ ለመርዳት እዚህ ይገኛል።
በአስቸኳይ የአደጋ ጊዜ ላይ ከሆኑ፣ በሦስት ዜሮ (000) ይደውሉ።

ኦሬንጅ ዶር የሚከተሉትን ከሆኑ ሊረዳዎ ይችላል፦
 • በወላጅነት ዙርያ እገዛ ከፈለጉ፣ ወይም ስለ ህጻን ወይም ወጣት ልጅዎ ደህንነት ወይም እድገት የሚጨነቁ ከሆነ።
 • ለእርስዎ ቅርብ የሆነ ሰው እንደ አጋርዎ፣ የቀድሞ አጋርዎ፣ የቤተሰብ አባልዎ ወይም ተንከባካቢዎ ያሉ ፍርሃት ወይም ስጋት እንዲሰማዎት እያደረገ ከሆነ።
 • ደህንነት የማይሰማዎት ወይም የሚንከባከብዎት የሌለ ልጅ ወይም ወጣት ከሆኑ።
 • የመሳደብ ወይም የመቆጣጠር ባህሪን የመጠቀም አደጋ ላይ ከሆኑ ወይም በቤት ውስጥ ወይም በግንኙነት ውስጥ በእነዚህ ባህሪዎች ላይ እገዛ ከፈለጉ።
 • ስለሚያውቁት ሰው ደህንነት ከተጨነቁ።
 • የት እንደሚሄዱ፣ ማንን እንደሚያገኙ ወይም እንዴት ገንዘብ እንደሚያጠፉ የሚከታተልዎ ሰው አይነት ባህሪን ጨምሮ የቤተሰብ ጥቃት ካጋጠሞት።

ኦሬንጅ ዶር የሚከተሉትን በማድረግ ሊረዳዎ ይችላል፦
 • እርስዎን በማዳመጥ እና ጭንቀቶችዎ ምን እንደሆኑ በመስማት።
 • የሚፈልጉትን እርዳታ እና ድጋፍ ለመለየት ከእርስዎ ጋር አንድላይ በመስራት።
 • በልጆች እና ወጣቶች ደህንነት እና እድገት እርስዎን በመደገፍ።
 • የእርስዎን እና የልጆችዎን ደህንነት ለመጠበቅ የደህንነት እቅድ እንዲያዘጋጁ በማገዝ።
 • እርስዎን ሊያግዙ ከሚችሉ አገልግሎቶች ጋር በማገናኘት፣ እንደነ የምክር አገልግሎት፣ የመኖርያ ቤት፣ የቤተሰብ ጥቃት ድጋፍ፣ የአእምሮ ጤና እና የአደንዛዥ ዕፅ እና የአልኮል አገልግሎቶች፣ የወላጅነት ድጋፍ ቡድኖች፣ የልጆች አገልግሎቶች፣ የገንዘብ እርዳታ ወይም የህግ ድጋፍ።
 • ለመሠረታዊ የኑሮ ወጪዎች እና ሌሎች ወጪዎች የገንዘብ ድጋፍ እንዲያገኙ በመደገፍ።
 • በቤት ውስጥ ወይም በግንኙነት ውስጥ ተሳዳቢ ወይም ቁጥጥር የማብዛት ባህሪን እየተጠቀሙ ከሆነ እንዲቀይሩ ለመርዳት ከእርስዎ ጋር በመስራት።

ኦሬንጅ ዶርን እንዴት መጠቀም እችላለሁ?
ኦሬንጅ ዶር ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 9 ሰአት እስከ ከሰአት ቡሃላ 5 ሰአት ክፍት ነው (በህዝባዊ በዓላት ዝግ ነው)።

የአካባቢዎን አገልግሎት ለማግኘት በቦታ ወይም በፖስታ ኮድ ይፈልጉ

የመግባብያ መሳሪያዎችን የሚጠቀሙ ከሆነ ወይም የምልክት ቋንቋን ጨምሮ አስተርጓሚ ከፈለጉ The Orange Door ከእርስዎ ጋር ሊሰራ ይችላል።

አስተርጓሚ እፈልጋለሁ
አስተርጓሚ እንደሚፈልጉ አገልግሎቱን ያሳውቁት። አገልግሎቱን የሚከተሉትን ያሳውቁት፡-
 • የስልክ ቁጥርዎን
 • ቋንቋዎን 
 • ለመደወል ደህና የሚሆንበት ጊዜ። 

ከዚያ አስተርጓሚ መልሶ ይደውልልዎታል። 

ኦሬንጅ ዶር ለእኔ የተነደፈ አገልግሎት ነውን?
የኦሬንጅ ዶር በማንኛውም እድሜ፣ ጾታ፣ ጾታዊ ዝንባሌ፣ ባህል እና ችሎታ ያሉ ሰዎችን በደስታ ይቀበላል። ሁሉም ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ ምርጫዎች የተከበሩ ናቸው። ከወንድ ወይም ከሴት ሠራተኛ ጋር መሥራት ከመረጡ ለሠራተኛው ያሳውቁ። የኦሬንጅ ዶር የግለሰቦችን እና ቤተሰቦችን የተለያዩ ፍላጎቶች ለማሟላት ከመድብለ ባህላዊ አገልግሎቶች፣ የኤልጂቢቲአይ (LGBTI) አገልግሎቶች እና የአካል ጉዳት አገልግሎቶች ጋር ይሰራል። ሰራተኞች ስላሉት አማራጮች መረጃ ይሰጡዎታል እንዲሁም ከሚፈልጓቸው አገልግሎቶች ጋር ያገናኙዎታል።

ስደተኛ ከሆኑ ወይም ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ከሌለዎት አሁንም ልንረዳዎ እንችላለን። በመኖሪያ ፍቃድዎ ሁኔታ ምክንያት ድጋፍ ለመጠየቅ አይፍሩ፣ ይህ ነፃ አገልግሎት ነው። ስለ ሁኔታዎ በስልክ ወይም በአካል መወያየት ከመረጡ የኦሬንጅ ዶር ሰራተኞችን ያሳውቁ።

የኦሬንጅ ዶር ክፍት ካልሆነ የት መሄድ አለብኝ?  
ከእነዚህ ሰዓቶች ውጭ የሚከተሉትን አገልግሎቶች ያግኙ፡-
 • የወንዶች ሪፈራል አገልግሎት/Men’s Referral Service በ 1300 766 491 (ከጠዋቱ 8 ሰዓት እስከ ምሽቱ 9 ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ከጥዋቱ 9 ሰዓት እስከ ምሽቱ 6 ሰዓት ቅዳሜ እና እሑድ ብሎም ህዝባዊ በዓላት) (የወንዶች ቤተሰብ ጥቃት የስልክ ምክር፣ መረጃ እና ሪፈራል አገልግሎት)
 • ሴፍ ስቴፕስ (Safe Steps) የቤተሰብ ጥቃት ሰለባ ለሆኑ የድጋፍ አገልግሎት ነው በ1800 015 188 (24 ሰዓታት በሳምንት 7 ቀናት) ይደውሉ። እንዲሁም ሴፍ ስቴፕስ (Safe Steps) በኢሜል መላክ ወይም የቀጥታ የድረ-መስመር ውይይት (ዌብ ቻት) ድጋፍ አገልግሎታቸውን መጠቀም ይችላሉ።
 • የወንጀል ተጎጂዎች የእርዳታ መስመር (Victims of Crime helpline) (ለወንጀል ሰለባ ለሆኑ እና ለቤተሰብ ጥቃት ሰለባ ለሆኑ አዋቂ ወንዶች)    1800 819 817 ወይም በ 0427 767 891 የጽሑፍ መልእክት ይላኩ (ከጥዋት 8 ሰዓት እስከ ምሽቱ 11 ሰዓት፣ በየቀኑ)
 • የወሲብ ጥቃት ቀውስ መስመር (Sexual Assault Crisis Line) ለጾታዊ ጥቃት ሰለባዎች ነው 1800 806 292 (በሳምንት 24 ሰዓታት፣ 7 ቀናት)

እርስዎ ወይም ሌላ ሰው አፋጣኝ አደጋ ውስጥ ከሆኑ፣ ለድንገተኛ እርዳታ ሶስት ዜሮ (000) ላይ ይደውሉ። 

ግብረመልስና እና ግለ-ሚስጥር
ስለ ኦሬንጅ ዶር ያለዎትን ልምድ በ orangedoor.vic.gov.au/feedback በሚገኘው የኦንላይን አስተያየት መስጫ ቅጽ በመጠቀም ወይም በ1800 312 820 በመደወል እና ሰራተኛዎን፣ ተቆጣጣሪውን ወይም ስራ አስኪያጁን እንዲያነጋግሩ በመጠየቅ አስተያየት መስጠት ይችላሉ።

ለግል ሚስጢርዎ ቦታ እንሰጣለን። የእርስዎን መረጃ እንዴት እንደምንጠቀም ለማወቅ ከፈለጉ፣ እባክዎ የግለ-ሚስጢር ኣጠባበቅ ፖሊሲያችንን ይመልከቱ።